ሊባኖስ እና መቆምያ የሌለው የኢትዮጵያውያን ፍልሰት

https://fb.watch/5LoJmb1KMq/

ወደ ሊባኖስ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን መምጣት ከጀመሩ በዛ ያሉ አስርት አመታት እንዳለፉ እሙን ነው። በነዚህ ግዜያትም ለቁጥር የሚታክቱ ዜጎቻችን አልፈዋል አካለ ጎዶሎ ሆነዋል አዕምሯቸውን ስተው ወደ አገራቸው ገብተውል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ልጆች ከሌላ አገር ዚጋ ወንዶች ተወልደው በተለያየ መንገድ ወደ አገር ገብተዋል። 

ከምንም እና ከምንም ኢትዮጵያችን ከነዚህ ህይወታቸውን እየገብሩ ከሚኖሩ ልጆቿ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገቢ በማግኘቷ ዜጎች (ቤተሰቦች) ህይወታቸው ከቀድሞ በተሻለ እንዲሆን ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሰናል። አገራችንም በነዚሁ ዜጎቿ በሚላከው ገንዘብ ተተቃሚ ሆና የኢኮኖሚ አውታሮቿ ሲደገፉ ቆይተዋል አሁንም እየተደገፉ ነው።

ሊባኖስ የምትወደድ እና በተለይ የነጭ  ባህርን ጠር ተከትላ የተመሰረተች አገር በመሆኗ የቱሪስቶች መስዕብ ሆና ለበርካታ ዘመናት ኖራለች። ምንም እንኳን የእርስበዕርስ ጦርነቱ አገሪቷን ወደ አመድነት ቅቀይሯት የነበረ ቢሆንም በወቅቱ በነበሩ መሪዎቿ እንደገና አንሰራርታና ተገንብታ አሁን ላላት ውበት በቅታለች።

እንግዲህ ከላይ በመጣሁበት መንገድ የምንሄድ ከሆነ አሁን በትክክል በዚህች በሊባኖስ እና በኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን ተቃርኖ መገመት አይቻልምን ወደሱ ልግባ። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ይች አገር በኢትዮጵያውያን እጅጉን ተጠቅማለች አሁን እየተጠቀመች ነው። ኢትዮጵያችንም በነዚሁ ተመሳሳይ ሰዎች እጅጉን ተጠቅማለች እየተጠቀመችም ነው። በተለያዩ ግዜያትም እነዚሁ ስደተኞች ወዲች ሊባኖስ የምትባል አገር ምንም አይነት የስራ፣ የኢኮኖሚም ይሁን የፖለቲካ ስምምነት ባለመኖሩ የጉዞ እገዳ የጣለች ቢሆንም ኢትዮጵያውያኑ ግን ከመሰደድ ሊገታቸው እና ሊአስቆማቸው አልቻለም። ተስፋቸው እና የወደፊት እጣ ፋንታቸው በዚህች አገር መዝገብ ላይ ብቻ የተጻፈላቸው ይመስል እንደጎርፍ እየተጓዙ መምጣቱን ተያይዘውታል። ከቅርብ አመታት (ከ2019 መጀመርያ) አንስቶ አገሪቷ በፖለቲካዊ እና በኢትኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ በመግባቷና የኮሮና በሽታም ባስከተለው የእንቅስቃሴ እገዳ በኢኮኖሚዋ ቁልቁል እየተጓዘች ያለች አገር ሆናለች። ዜጎቿ በዚሁ ችግር የተነሳ ገንዘባቸውን ካስቀመጡበት ባንክ የማውጣት እገዳ ተጥሎባቸው ሃብት ሳያጡ ለረሃብና ለእርዳታ ተጋልጠው ይገኛሉ። በርግጥ በተለያዩ ቦታዎች ውስን እንቅስቃሴ ቢኖርም የቀድሞው አይነት መንፈስ ባለመኖሩ ከዛሬ ነገ አገሬው ቤቱን ጥሎ ሆ ብሎ ወጥቶ ከዚህ ቀደም የነበረው ጦርነት ውስጥ ይገባል እየተባለ ይፈራል።

ታድያ በዚህ ሰዎች ከቤታቸው ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው እየተገፉ በሚወጡበት ወቅት፣ ስደተኞች ለሰሩበት ደሞዛቸውን ከአመትና እና ከዛ በላይ ሳይከፈላቸው በግዞት(በባርነት) እየኖሩ ባለበት ወቅት፣ ሴቶች ለራሳቸው መሆና ባቃታቸው በዚህ ሰአት አርግዘው በድህነትና በስቃይ ወልደው ለማሳደግ በሚንገዳገዱበት ወቅት፣ ቤተሰብ ሳይወድ በግዱ ተከፋፍሎ መኖር በጀመረበት ወቅት፣ ስደተኞች በተለያዩ መንገዶች በህገወጥ ለባርነት እና ለሴተኛ አዳሪነት በተጋለጡበት ወቅት፣ ሃይ ባይ ጠፍቶ፣ ከልካይ መላሽ አስተባባሪ ጠፍቶ፣ ተቆርቋሪ ጠፍቶ ወደዚህች ምስቅልቅሏ ወጥቶ የሚበላ ተለምኖ መበላት በተጀመረበት በዚህ ግዜ ፣ህጻናት ተመጣጣኝ ምግብ እና የጽዳት እቃዎቻቸው ከገበያ ጠፍተው ቤተሰብ ለችግር በተጋለጠበት በዚህ ግዜ የኢትዮጵያ መንግስት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና በየክፍለሃገሩ ያሉ ደላሎችን መግብያ መውጫ አሳጥቶ በህግ የማያዳግም ቅጣት ጥሎ ማስቆም ያልቻለበት ምክንያት ይገርመኛል።

ወደሊባኖስ የሚመጡት ኢትዮጵያውያን ከገጠራማው አካባቢ የሚመጡ በመሆናቸው ደላሎቹ የኢነግሯቸውን ነገር ብቻ ለማመን ቀላል በመሆናቸው ራሳቸው ለስደት ቅርብ ያደረጉ ናቸው። ለውጥን በቀላሉ ለማግኘት ያለምጁ በመሆናቸው ወደፊት መሄድ እንጂ ለምን እና እንዴት ብለው አይጠይቁም። በተቃራኒው ቤተሰቦቻቸውን አራቁተው ነው ለስደት የሚነሱት።

foto by Genet(buze)፡ The ways of modern slavery rootine in Lebanon
foto by Genet(Buze) : The ways of modern slavery rootine in Lebanon

እነሆ ከላይ ያሉት ፎቶውዎች በ28/4/ 2021  ከኢትዮጵያ በትራንዚት የመጡት ኢትዮጵያውያን እንደ ማስረጃ ይያዝልኝ እና እነዚህን ልጆች በስራ ቪዛ ወደ ሊባኖስ የሊባኖስ መንግስት ሲያመጣቸው የአገራችን መንግስት ምን እየጠበቀ ነው? ለመሆኑ የሊባኖስ ነባራዊን ሁኔታ ቆንስላው ግናዛቤ መስጨበጫዎችን አይልክም ወይ?  ምን አይነት ችግር ውስጥ እንደሆነ ይህ ሚሲዮች ለበላይ አካላቶች የሚያስተላልፈው ነገር የለም ወይ? መንግስት በየየአገሩ ክፍሎች እየሄደ የፖለቲካ አጀንዳውን በኢትዮጵያችን ሏላዊነትም ሆነ በዲፕሎማሲው ረገድም ምንም አይነት ተጸእኖ ሊፈጥሩ የማይችሉትን የየአካባቢ አመራሮችን ሰብስቦ ስለአባይ ግድብ ከማስገንዘብ በተሻለ ኢትዮጵያን ከውጪ ወራሪም ሆነ አገሪቱን እንደ አገር ሊያቆዩዋት ስለሚችሉት ህዝቦቿ ጥብቅና ቢቆም እና እነዚህንም ዜጎቹን በዘመናዊ ባርነት እየተቸበቸቡ ካሉበት ገበያ ሊያድናቸው ይሻላል ባይ ነኝ። ከሊባኖስ ልናገኝ የምንችለው ምንም አይነት የፖለቲካ ድጋፍ  ይኖራል ብዬ አላስብም። አንድ አገር እንደ አገር ተመስራታ ባለችበት መንግሥት አላት ተብሎ በሱም እየተመራች ባለችበት ዜጎች መብታቸው እና ከአደጋም ሊጠበቁ ካልቻሉ አገርና መንግስት የሚባለው አካል ፋይዳቸው ምንድነው? እውነት ነው ዜጎቻችን በስደት ከሚኖሩባት ሊባኖን ውስጥ ለመስማት የሚከብዱ ስራዎች እና መጡ ተግባር ላይም ያሉ እንዳሉ ግልጽ ነው። ነገር ግን ችግሩ ወደ ስደት ከመውጣታቸው በፊት ተቀርፎ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ ባልተከሰተ ነበረ። በሊባኖስ ያለውም ቆንስላ ስራው ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ እንዳይሆን በየቀኑ እየተጋዙ የሚመጡትን ዜጎች ለምን እና እንዴት ሊገቡ ቻሉ ብሎ ይጠይቅ። በሊባኖስ መንግስት ላይ እንደ አገር ጫና ፈጥሮ ይሄንን የመነሻ አገር ፈቃድ ሳይጠይቅ ዜጎቹን ለስራ በሚል ቪዛ ለባርነት እያግበሰበሰ ማምጣቱ እንዲያቆም ማስደረግ። ማንም ኢትዮጵያዊ ለጉብኝት ወደ ሊባኖስ አይመጣምና።

ለዛሬው ጨረስኩ እስከዛው ግን ቸር ሰንብቱ።

መስዋዕት ለዜጎቹ ይቆማል

ኢትዮጵያም በዜጎቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች።

Published by Mesewat

Mesewat is a non-governmental, non-religious, non-racial and non-profit solidarity network that supports migrant workers in Lebanon and the Middle East.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: