እንደሚታወቀው በሊባኖስ ከሌላው ስደተኛ በላቀ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን በየአካባቢው እንገኛለን። ነገር ግን እንደ ብዛታችን መጠን ምንም ደጋፊ እና ከጎናችሁ ነን፣ ነኝ ባይ ቢኖርም ችግራችን ግን ከቁጥራችን ገዝፎ ይገኛል። በከፍተኛ ሁኔታ በአሁን ሰአት በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ደሞዝ ያለመከፈል ነው። ይህንን ደሞዝ ያለመከፈል ችግር ትኩረት ሰጥቶ ለተበዳይ ፍትህን ለማሰጠት ጥረት የሚያደርጉ ቢኖሩም አባይን በጭልፋ እንዲሉ እህቶቻችን ያለ ፍላጎታቸው በአሰሪዎቻቸው ቤት ውስጥ ለአመታት በነጻ ያለምንም ክፍያ ጉልበታቸው እየተበዘበዘ ይገኛል።
ከአንድ አመት እስከ 8 አመት ደሞዝ ያለመከፈል ችግር በለባት አገር ሰሞኑን እያየን ያለው ወደ ሊባኖስ የሚደረግ ጉዞ አሁን ባለብን ችግር ላይ ሌላ ከፍተኛ የሆነ ችግር እየመጣብን እንደሆነ ማሳያ ነው። በሊባኖስ ያለው የኢኮኖሚ ችግር ዜጎቹ እንኳን ለሰራተኛ መክፈል አይደለም ለራሳቸውም ልመና እየገቡ እንደሆነ ብዙ ማሳያዎች አሉ። እርግጥ ነው እስካሁንም በዶላር እና በሊባኖስ ፓውንድ እየተከፈላቸው ያሉ ብዙ እህቶች እንዳሉ እሙን ነው። ነገር ግን ያለውን ችግር መሸፈን ስለማይችል ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቁ የችግሩን ስፋ እንዲመለከቱና መፍትሄ እንዲያበጁ መንገድ ይሆናል።
ቀደም ባሉት ግዜያት ብዙዎች በተለያዩ አካላትና ህጋዊ ተቋማት አማካኝነት ያልተከፈለ ደሞዛቸው እንዲከፈል እየተደረገ የቆየ ቢሆን አሁን ባለው ተጨባጭ የአገሪቱ ሁኔታ የነዚህን በግፍ በዘመናዊ ባርነት ቀንበር ውስጥ ያሉ እህቶቻችንን ላብ ማስከፈል አዳጋች ሆኗል።
በመሆኑም የሁለቱም አገራት መንግስታት የነዚህን በላባቸው እያደሩ ያሉትን ወጣት ኢትዮጵያውያን ሴቶችም ሆነ የሌላ አገር ስደተኞችን እንግልት እና ስቃይ በመነጋገር መፍታት የሚችሉበትን እና ወደ አገራቸውም እየተመለሱ ላሉ ተመላሽ ስደተኞች በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅ የአረብ አገራት በመልሶ ማቋቋም ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉ ዳግመኛ ለስደት እንዳይነሱና በአገራቸው ላይ ሰርተው ራሳቸውንም ሌሎችንም ለመቀየር የሚያስችል መፍትሄ ነው ብለን እናስባለን።
በልባኖስ ያለውን የዜግኅችን የነጻ ባርነትን አጥብቆ ልመከላከል።
LikeLiked by 1 person
ከአገር ቤት እስከ ተቀባይ አገር ጠንቃራ መዋቅር ተጥሎ መሰራት ይኖርበታል። መንግስታችን በየስርቻው የእህቶቻችንን አይምሮ በሃሰት ተስፋ በመሙላት ኪሳቸውን እየሞሉ ያሉት ደላሎች ከስራቸው መንግሎ መጣል ይገባዋል። አልያ ግን ስደትን መግታት ባይቻልም የእህቶቻችንን ህይወት ማታደግ ወደ ማንችልበት ከባድ ችግር የሚወስደን መንገድ ውስጥ መሄዳችን በስፋት ይቀጥላል።
LikeLike